አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ፖለቲካ / ምርጫ

ኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ልምምድ አርአያነቷን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አረጋገጠች

በአዳሙ እርቅይሁን | July 4, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

ኢትዮጵያ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያሳየችው ህዝባዊ ተሳትፎ እና የዲሞክራሲ ሂደት፣ ለአፍሪካ ሀገራት አዲስ ተስፋን የፈነጠቀና ለሌሎችም አርአያ የሚሆን መሆኑን የአፍሪካ ህብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ገለጹ።

በምርጫው ሂደት በታዛቢነት የተሳተፉት እነዚህ ተቋማት፣ ኢትዮጵያ የአህጉሪቱን የነጻነት ተምሳሌትነቷን በድጋሚ ማረጋገጧን በግልጽ አስታውቀዋል። ታዛቢዎቹ እንደገለጹት፣ የምርጫ ጣቢያዎች በተቀመጠላቸው ሰዓት ሥራቸውን መጀመራቸው፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችም በሙያዊ ሥነ-ምግባር ታንጸው ግዴታቸውን መወጣታቸው ለሂደቱ ስኬታማነት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ እንደሆነ በምልከታቸው የገለጹት ታዛቢዎቹ፤ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና እናቶች በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን ሲሰጡ መታዘባቸውን አስታውቀዋል። ይህ ህዝባዊ ተሳትፎ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መሰረት ከመሆኑም በላይ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሊማሩበት የሚችል ተሞክሮ መሆኑ ተመላክቷል።

ታዛቢዎቹ አክለውም፣ ዜጎች በዲሞክራሲያዊ ልምምድ ውስጥ ያላቸው ንቁ ተሳትፎ የራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰን መብት መገለጫ እንደሆነ ገልጸዋል። "የራስ እድልን መወሰን ማለት የህዝብ እንጂ የመሪዎች ብቻ አይደለም፤ ኢትዮጵያውያን በምርጫ ካርዳቸው ያሳዩት ተሳትፎም ይህንኑ የዲሞክራሲ እሴት የሚያንጸባርቅ ነው" ብለዋል።

በተዘዋወሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ የተመለከቱት ሰላማዊ ድባብ እና የህዝቡ በትዕግስት መሰለፍ፣ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርአት እየተጠናከረ መምጣቱን የሚያሳይ ተጨባጭ ማረጋገጫ እንደሆነ ታዛቢዎቹ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ባለሙያዎች የነበራቸው ሙያዊ ዝግጁነት እና ቅልጥፍናም በታዛቢዎቹ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።

በአጠቃላይ፣ ይህ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየችበትና ለአፍሪካዊያን የነጻነት ትግል ውጤት አርአያ የሆነ ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ ፍላጎቱን በተግባር የገለጸበት መንገድ፣ ለሀገሪቱ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ መረጋጋት እና የልማት ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ