አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ሳይንስ / ቴክኖሎጂ

​የናሳው «ኩሪዮሲቲ» ሮቨር በማርስ ላይ ሰፊ የማር እንጀራ መሰል የጂኦሜትሪ ንድፍ አገኘ

በዳንኤል ግዛው | August 1, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) የ «ኩሪዮሲቲ» (Curiosity) መንኮራኩር/ሮቨር በማርስ ፕላኔት ላይ እስከ አድማስ ድረስ የተዘረጋ እና የማር እንጀራ ቅርጽ ያለው ሰፊ የጂኦሜትሪ የመሬት አቀማመጥ ማግኘቱን አስታወቀ።

\r\n

​ሳይንቲስቶች እንደገለጹት፤ ከተቋሙ የቀደሙ የጠፈር ተልዕኮዎች ጋር ሲነጻጸር አሁን በማርስ ላይ የተገኘው የጂኦሜትሪ ንድፍ በስፋቱና በስርጭቱ አቻ የሌለው ነው።

\r\n

​«ቫሌ ግራንዴ» (Valle Grande) በተሰኘው የማርስ ሸለቆ ውስጥ የተደረገውን አሰሳ ተክተሎ የተላኩት ምስሎች ከ1.5 እስከ 3 ኢንች (ከ4 እስከ 8 ሴንቲሜትር) ስፋት ያላቸው ባለብዙ ማዕዘን (Polygonal) ስንጥቆች መኖራቸውን ያሳያሉ።

\r\n

​በተልዕኮው 4,930ኛ እና 4,931ኛ የማርስ ቀናት (ሶል) በተነሳው የ360 ዲግሪ ምዝግብ ምስል ላይ፣ እነዚህ አወቃቀሮች በሁሉም አቅጣጫዎች የተዘረጉ ከመሆናቸውም በላይ «ሚራፍሎሬስ» (Miraflores) በተሰኘውና 20 ጫማ (6 ሜትር) ቁመት ባለው አሸዋማ ኮረብታ ዙሪያ የተጠቀለሉ ሆነው ተገኝተዋል።

\r\n

​በናሳ የጄት ፕሮፐልሽን ላቦራቶሪ የፕሮጀክቱ ዋና ሳይንቲስት አሽዊን ቫሳቫዳ እንደገለጹት፤ የምርምር ቡድኑ በኩሪዮሲቲ ካሜራዎች በርካታ አስደናቂ የተፈጥሮ አቀማመጦችን የተመለከተ ቢሆንም፣ አሁን የተገኘው ሰፊ የጂኦሜትሪ ንድፍ ግን በተለየ ሁኔታ ቀልብ የሚስብ ነው። ሳይንቲስቶቹ የተሰበሰቡትን ኬሚካላዊ እና መዋቅራዊ መረጃዎች በመተንተን ቅርጹ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ ምስጢሩን ለመፍታት እየሰሩ ይገኛሉ።

\r\n

​እንደ ናሳ ገለጻ፤ ቀደም ሲል በፕላኔቷ ላይ የታዩ ተመሳሳይ ቅርጾች በውሃ መድረቅ ምክንያት ከተፈጠሩ የጭቃ ስንጥቆች (mud cracks) ጋር የሚመሳሰሉ ቢሆኑም፣ የአሁኑ አወቃቀር ግን በተለያዩ የተፈጥሮ ሂደቶች—ለምሳሌ በቅዝቃዜና በሙቀት መለዋወጥ ዑደት ወይም ደለል በሚጨመቅበት ወቅት ውሃ ተጭኖ በመውጣቱ ምክንያት ሊፈጠር እንደሚችል ይገመታል።

\r\n

​ምንጭ፦ ናሳ / ሳይንስ ዘገባ

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ