አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ቢዝነስ / ንግድ

ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂ ከ75 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ነው

በማስረሻ ቢተዉ | July 4, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

 ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅና ኢነርጂ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂ (TotalEnergies) በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን የሰባ አምስት ዓመታት ረጅም የአገልግሎት ቆይታ አጠናቆ ከአገሪቱ ገበያ ሙሉ በሙሉ ሊወጣ መሆኑ ተሰማ። ኩባንያው በአገሪቱ ውስጥ የነበሩትን ሁሉንም ንብረቶች ለማዛወር ወስኗል።

​የአፍሪካ ቢዝነስ ድረ-ገጽ እንደዘገበው፣ ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሃያ (220) የሚያህሉ የነዳጅ ማደያዎቹን፣ ቀደም ሲል በስሙ "ኦይል ሊቢያ" (OilLibya) ተብሎ ይጠራ ለነበረው ኦአይኤልኦ (Oilibya/OLA Energy) ኩባንያ ለመሸጥ የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል።

ቶታል ኢነርጂ ከነዳጅ ማደያዎች በተጨማሪ የተለያዩ የፔትሮኬሚካል ምርቶችን በስፋት ለኢትዮጵያ ገበያ በማቅረብ የሚታወቅ አንጋፋ ኩባንያ ነበር።

​ሆኖም ግን ሁለቱ ኩባንያዎች ስለ ሽያጩና ንብረት ግዢ ስምምነት ዝርዝር ሁኔታ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም። በኢትዮጵያ የነዳጅ ስርጭት ገበያ ውስጥ ካሉት ግዙፍና ቀዳሚ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች መካከል ቶታል ኢነርጂ፣ ኦአይኤልኦ (OLA Energy)፣ ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (NOC) እና የኢትዮጵያ የተባበሩት ነዳጅ ኩባንያዎች (የቶታል አጋሮች) ዋና ዋናዎቹ ተጠቃሽ ናቸው።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ