አምዶች
የቅርብ ዜና
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ዞን በተፈጸሙት ጥቃቶች ላይ ያወጣው የሐዘንና የተቃውሞ መግለጫ • አርሰናል ኤቨርተንን ካሸነፈ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አናት ተሸጋገረ • የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተቋቋመ፤ ዋና አስፈጻሚዎችም ተሾሙ • በትግራይ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ፈራርሷል፣ ጦርነት እንደገና ተቀስቅሷል • ህንድ በኒው ዴልሂ በተደረገው ዘመቻ ‘ኮክሮች’ የተሰኙ የመብት ተሟጋች መሪዎችን ጨምሮ 2,000 ሰዎችን አሰረች • ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ ስምምነት ዘሌንስኪን በሌላ መሪ እንድትተካ ጥሪ አቀረቡ • የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ደገፉ፤ በትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ተግዳሮቶች ላይም አመለከቱ • ኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መሠረተች፤ የፓርላማ ዋና ዋና አመራሮችና ጠቅላይ ሚኒስትር ተሾሙ • ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች፤ ኤርትራውያን ዲፕሎማቶችም ከአገር እንዲወጡ አዘዘች • ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው በድጋሜ ተሾሙ • የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአርሲ ዞን በተፈጸሙት ጥቃቶች ላይ ያወጣው የሐዘንና የተቃውሞ መግለጫ • አርሰናል ኤቨርተንን ካሸነፈ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አናት ተሸጋገረ • የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተቋቋመ፤ ዋና አስፈጻሚዎችም ተሾሙ • በትግራይ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ፈራርሷል፣ ጦርነት እንደገና ተቀስቅሷል • ህንድ በኒው ዴልሂ በተደረገው ዘመቻ ‘ኮክሮች’ የተሰኙ የመብት ተሟጋች መሪዎችን ጨምሮ 2,000 ሰዎችን አሰረች • ትራምፕ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ ስምምነት ዘሌንስኪን በሌላ መሪ እንድትተካ ጥሪ አቀረቡ • የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ደገፉ፤ በትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ተግዳሮቶች ላይም አመለከቱ • ኢትዮጵያ አዲስ መንግሥት መሠረተች፤ የፓርላማ ዋና ዋና አመራሮችና ጠቅላይ ሚኒስትር ተሾሙ • ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች፤ ኤርትራውያን ዲፕሎማቶችም ከአገር እንዲወጡ አዘዘች • ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆነው በድጋሜ ተሾሙ
ፖለቲካ / የፖለቲካ ፓርቲዎች

የዜጎች ክብር የዲፕሎማሲያችን ኹሉ ቊንጮ ይኹን

July 4, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለሰቆቃ ስለተጋለጡ ዜጎች የተሰጠ መግለጫ።

ኢትዮጵያዊያን በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ያለ ቪዛ ወደ ውጪ አገር ለትምህርት በሚላኩበት ወቅት ፈተናቸውን አልፈው የምረቃ ሥነሥርዓት እንኳን ሳይጠብቁ ተሳፍረው ወደ አገራቸው ይመለሱ ነበር። ኢትዮጵያ ከምእራቡ ዓለም ጋር ሲነጻጸርም ደካማ የኢኮኖሚ ደረጃና የማኅበራዊ ግልጋሎትም አልነበራትም። የምእራቡ ዓለም ምቾት የአገር ፍቅርንና የእናት ቤት ሽሮን የሚያስንቅ አልነበረም። አንድ ሰው ከተማረ ተከብሮ አገሩ ያገለግላል። ማኅበረሰቡም ይኮራበት ነበር።

ይኹንና በመጨረሻው ያለንን ኹሉ አፍርሰን እንደ ቻይናና ሦቪዬት ኅብረት ሦሻሊዝምን፣ የስታሊንን የብሔር ብሔረሰቦች ፓለቲካ ብንተክል የተሻለ እንኾናለን ተባለ። ያም ኢትዮጵያን ወደ ምድራዊ ሲዖል ቀየረ። ስደት እንደ ጌጥና ልዩ እድል ተቆጠረ። አዛውንቶችንና አርበኞችን በጅምላ መረሸን፣ ወጣቱን በቀይ ሽብር መጨረስ እድል ፈንታችን ኾነ። በዚያም ሳይበቃ ቀጥሎ የመጣው ደግሞ መጤ፣ ነፍጠኛ፣ ኦርቶዶክስ፣ ሴማቲክስ እያለ ምድሪቷን በደም አጠባት። ምንም የማያውቁ ሕጻናት ለሰቆቃ የሚዳረጉበት፣ እርጉዝ እናት በአሰቃቂ የምትገደልበት ዘመን መጣ፣ አለ፣ ደርሰን ካላስቆመነው ይቀጥላል።

ይኽን ግፍና አድሏዊነት ፈርቶ የሚሸሸው ከመጥበሻው ወደ እሳቱ፣ ጅብ ፈርቸ ዛፍ ብወጣ ነብር ቆዬኝ እየኾነ መጣ። እስከአኹን በወጣ ይፋዊ መረጃ በዚኽ ሣምንት ብቻ ከ7 በላይ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን Xenophobia(መጤ ጥላቻ) በተሰኘ ዘመናዊ አፓርታይድ አስተሳሰብ ወንድሞቻችን በአሰቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል። ትናንት ለአፍሪካውያን ከባርነትና ነጻነት በተለይ ለደቡብ አፍሪካውያን የበዛ ግፍ አገዛዝ ለማላቀቅ እነኔልሰን ማንዴላን ዜግነት ሰጥታ፣ ወታደራዊ ስልጠና፣ ስንቅና ትጥቅ ቋጥራ ለነጻነት ጎሕ የቀደደች አገር ዜጎች ለውለታቸው መታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸው በድባብና ቀይ ምንጣፍ መሄድ ሲገባቸው በጉልበታቸው ጥረው ግረው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያን መሳደድና መገደል እጅጉን አስቆጥቶናል፤ ለፀፀት ዳርጎናል። ትብብራችን በግፍና በደቦ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ልባዊ ሐዘኑን ይገልጻል። 

በሌላ በኩል በሳውዲ አረቢያ ምድር በአገሬው ሕግ(ሸሪዓ) መሠረት ከ 60 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ እንዳለ ዓለም አቀፍ ተቋማት ካወጡት ሪፖርት መረዳት ችለናል። ይኽም እንደዜጋና የሕዝብ ሕመም እንደሚሰማው ፓርቲ ልባችን ክፉኛ ተነክቷል። በእርግጥ ይሄ ስደተኞችን ምክንያት እየፈለጉ ማጥቃት በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣ አባዜ አካል ነው ብለን እናስባለን። ኢትዮጵያና ሳውድ አረቢያ ከንግድና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በዘለለ የቀደመ የሚባል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በሃይማኖት፣ በምግባር አገሩን ያቀኑበት ትስስሩን ያጎለበቱበት ይልቁኑም ኢትዮጵያ የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ተከታዮች የኾኑ ካዕባዎችን በአገራቸው በዕምነታቸው ምክንያት ተሳደው ሲመጡ ለዘር አትርፎ ያቆዬ ሕዝብና አገር ነው። በዚኽም ኢትዮጵያ እስልምናን ከመጥፋት የታደገች ግምጃ ቤት ናት ቢባል ማጋነን አይኾንም።

የዚኹ ውለታዋና ክብሯ እንደተጠበቀ ኾኖ የትኛውም ሰው በየትም ቦታ በወንጀል ከተገኘ በፍትሕ አደባባይ መቅረቡን በጽኑ የምናምነውና የምንከራከርለት መርሕ ቢኾንም እነዚኽ ኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻው የጭካኔ ፍርድ መፈጸሙን በጽኑ እንቃወማለን። ነገሩ በቅርብ ጊዜያት ወዲኽ እያቆጠቀጠ የመጣውን ስደተኛ ጠልነት ጋር የተገናኘ እንጂ በወንጀል  እንዳልኾነ ጥርጣሬው አለን። ይኽም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንደምንቆጥረው የሳውዲ መንግሥትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቅልን እንሻለን። 

ስለኾነም፣
1. የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በኢትዮጵያውያንና በመላው አፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የግፍ ግድያና ማሳደድ እንዲያስቆም ለሞቱትም አግባብ ያለውን ማቋቋሚያና ካሳ እንዲሰጥ አፍሪካ ሕብረትና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። 

2. የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን የግፍ ግድያ ማስቆም የድፕሎማሲ ሥራው ኹሉ ቊንጮ መኾኑን መረዳት አለበት ብለን እናምናለን። ውቂያኖስ አቋርጦ ስለሌሎች አገር ዜጎች መገደል ጥብቅና ሲቆም ያየነው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ይሄንን በጉያው የሚፈጸም የግፍ ግድያ ማስቆም ካልቻለ በአፍሪካ ኅብረት ያለውን ተሳትፎ ጭምር እንዲጤን ከሌሎች አፍሪካውያን ጋር በመኾን ግፊት እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን።

3. ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነትና የኢትዮጵያን ውለታ በማውሳት መንግሥት በመታረጃው ቄራ ቆመው የሞት አፋፍ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንዲታደግና ጣልቃ ገብቶ የሞት ፍርዱ ወደ እሥራት እንዲቀየር ብሎም በአገራቸው እንዲዳኙ አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ኹሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን። 

4. መንግሥት የችግሩ መነሻ የኾነውን፣ በአገር ውስጥ መኖር የማያስችሉና ለስደት የሚዳርጉ አገራዊ ቀውሶችን እንዲያስቆም እናሳስባለን። 

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
***

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ