አምዶች
የቅርብ ዜና
• በትግራይ ክልል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከተሎ የመገናኛ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋጧል • የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከመጀመሪያው ብሔራዊ ምርጫ በፊት የመንግሥትን መዋቅር በተኑ • ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት መስከረም 25 ቀን ሊመሠረት ነው • የሰባት አማፂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መስረታ እና በሰሜኑ የትግራይ ክልል የነገሰው አዲስ ውጥረት • ጉግል ጂሚኒ ኤአይ (Gemini AI) የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ሶስት ኩባንያዎችን ሰበረ • አብን በአማራ ተወላጆች ላይ የተቀናጀ ጥቃት እየተካሄደ ነው ሲል ከሰሰ • ኡበር አሽከርካሪው በሰከረች እንስት ላይ በፈጸመው ድርጊት የ40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት • አሜሪካ በኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት እና ተቋማት ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ አንስታለች • የይቅርታው መልክዓ-ፅልመት፡ የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት እንዴት ይመዘናል? • ዶናልድ ትራምፕ፡ በሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኢራን «ልትሆን ትችላለች» አሉ • በትግራይ ክልል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ተከተሎ የመገናኛ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋጧል • የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከመጀመሪያው ብሔራዊ ምርጫ በፊት የመንግሥትን መዋቅር በተኑ • ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት መስከረም 25 ቀን ሊመሠረት ነው • የሰባት አማፂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መስረታ እና በሰሜኑ የትግራይ ክልል የነገሰው አዲስ ውጥረት • ጉግል ጂሚኒ ኤአይ (Gemini AI) የሳይበር ጥቃት በመፈጸም ሶስት ኩባንያዎችን ሰበረ • አብን በአማራ ተወላጆች ላይ የተቀናጀ ጥቃት እየተካሄደ ነው ሲል ከሰሰ • ኡበር አሽከርካሪው በሰከረች እንስት ላይ በፈጸመው ድርጊት የ40 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት • አሜሪካ በኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት እና ተቋማት ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ አንስታለች • የይቅርታው መልክዓ-ፅልመት፡ የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት እንዴት ይመዘናል? • ዶናልድ ትራምፕ፡ በሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኢራን «ልትሆን ትችላለች» አሉ
ፖለቲካ / መስተዳድር

አብን በአማራ ተወላጆች ላይ የተቀናጀ ጥቃት እየተካሄደ ነው ሲል ከሰሰ

በያፌት ግርማ | September 19, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ፣ በመንግሥት መዋቅርና ከታጠቁ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በማዕከላዊና በምዕራብ ኢትዮጵያ ወሰናማ አካባቢዎች በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት፣ የጅምላ እስራት እና የሕዝብ ቁጥር ስብጥር የመቀየር (Demographic Engineering) እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው ሲል ከሰሰ።

​እንደ አብን መግለጫ ከሆነ፣ የአማራን ሕዝብ በ"ነፍጠኛ" ስም በመፈረጅ ለረጅም ዘመን ሲፈጸምበት የቆየው ጥቃት አሁን በ"ፋኖ" ስም በአዲስ መልክ ተቀይሮ ቀጥሏል። ይህ የፖለቲካ ፍረጃ በአበሽጌ ወረዳ፣ በወልቂጤ ከተማ እንዲሁም በአዋሳኝ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን መዋቅራዊ በደል ለማድረስ፣ ንብረት ለመቀማትና ያለ አንዳች ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማሰር ሽፋን ሆኗል ብሏል።

​የፓርቲው መግለጫ በምዕራብ ሸዋ፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና በጅማ ዞኖች አዋሳኝ ቀጠናዎች የደረሰውን የደኅንነትና የሰብዓዊ መብቶች ውድቀት ያመላክታል። አካባቢው ላይ የሚገኙ የጸጥታና የአስተዳደር መዋቅሮች የሕዝቡን ሕጋዊ የራስ መጠበቂያ መሣሪያ በመገፈፍ ማኅበረሰቡን እንደ ኦነግ ሸኔ ላሉ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት አጋልጠው ሰጥተዋል ሲል ድርጅቱ ገልጿል። ለአብነትም በአመያ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ነፍሰጡር እናቶች፣ ሕፃናትና መነኮሳትን ጨምሮ በርካታ ንጹኃን ዜጎች መገደላቸውን አውስተዋል።

​በተጨማሪም ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በወልቂጤ እና በአበሽጌ አካባቢዎች ከ1,000 በላይ ሰላማዊ የአማራ ተወላጆች ታፍነው በወልቂጤ የሕዝብ አዳራሾችና በዋልጋ ማሰቃያዎች መታሰራቸውን መግለጫው ጠቅሷል። አፈናው ሆን ተብሎ በዋናው የእርሻ ወቅት መከናወኑ ምርት እንዲበላሽና ማኅበረሰቡ ለከፋ የኢኮኖሚ ውድቀት እንዲዳረግ አድርጎታል ብሏል።

​ከአካላዊ ጥቃቱ ባሻገር፣ የተፈናቀሉ አባወራዎችን መሬት ለባለሥልጣናትና ለባለሀብቶች በማደል የአበሽጌ ወረዳን አስተዳደራዊ ወሰን በኃይል የመለወጥ ሴራ እየተካሄደ መሆኑን አብን አስረድቷል። ይህንንም ድርጊት በሚዲያና በሶሻል ሚዲያ ተበዳይን የመክሰስ (victim-blaming) ዘመቻ በማስደገፍ እውነታውን የመሸፈን ሥራ እየተሰራ ነው ብሏል።

​በሁከቱ ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸውን የጉራጌና የኦሮሞ ተወላጆችን ጨምሮ የማንኛውንም ንጹኃን ዜጎች እንግልት እንደሚያወግዝ የገለጸው አብን፣ ዋናው ኃላፊነት ግን ጥቃቱን ባመቻቹና ዝምታን በመረጡ የመንግሥት መዋቅሮች ላይ እንደሚወድቅ አሳስቧል። በመሆኑም የፌደራል መንግሥት መዋቅራዊ እስራትን በአስቸኳይ እንዲያስቆም፣ የታሰሩትን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እና የተፈናቀሉትን ወደ ቀዬአቸው እንዲመልስ ጠይቋል።

​በመጨረሻም የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ገለልተኛ ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር (OHCHR) ገለልተኛ መርማሪ ቡድን በመላክ በዞኑ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣሩ አብን ጥሪ አቅርቧል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ