አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ዜና / እውነት ወይስ ሀሰት

ማስተርስ ዲግሪን ወደ 4 ዓመት ለማራዘም የተላለፈ አዲስ መመሪያ አለመኖሩን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ

በያፌት ግርማ | July 11, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የማስተርስ (የሁለተኛ ዲግሪ) ትምህርት የቆይታ ጊዜ ወደ አራት ዓመት ተራዝሟል በሚል በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱት መረጃዎች ፍፁም ሐሰተኛና የአረዳድ ችግር ያለባቸው መሆኑን የኢፌዴሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ገለጸ።

​የባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት ሰኞ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማቅረቡን ተከትሎ፣ “የማስተርስ ትምህርት ወደ 4 ዓመት ሊያድግ ይገባል” የሚሉ የተዛቡ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ሰንብተዋል።

​ባለሥልጣኑ በጉዳዩ ላይ በሰጠው ይፋዊ ማብራሪያ፤ በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው ወቅት ከኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ጋር የተያያዙ ቴክኒካዊ ሃሳቦች መነሳታቸውን ገልጿል። ይሁን እንጂ እነዚህን የውይይት ነጥቦች በስህተት በመረዳት መረጃው ተዛብቶ ለሕዝብ መቅረቡን አስታውቋል።

​“የሁለተኛ ዲግሪ (Master Degree) ትምህርትን በተመለከተ እስካሁን ምንም የተቀየረ ሕጋዊ ደንብ የለም፤ እየተዘዋወረ ያለው መረጃ የአረዳድ ችግር እንጂ ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሠረት የሌለው ነው” ሲል ባለሥልጣኑ በአፅንኦት ገልጿል።

​ኅብረተሰቡም ሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ መሰል ያልተረጋገጡ ወሬዎች ሳይደናገጡ፣ ትክክለኛውን መረጃ ከሕጋዊ ሰነዶች እንዲረዱ ባለሥልጣኑ አሳስቧል። ለዚህም እንደ ማሳያ የተጠቀሰው “የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብ ቁጥር 561/2016” መሆኑን ጠቅሶ፣ ማንኛውም የትምህርት ቆይታና የብቃት ደረጃ የሚወሰነው በዚህ ጸድቆ በሚገኘው ሕጋዊ ደንብ መሠረት ብቻ መሆኑን አስታውቋል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ