አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ዜና / ዓለም አቀፍ ዜና

በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ

በአዳሙ እርቅይሁን | August 20, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

በግብፅ ሰሜናዊ የባሕር ዳርቻ እየተገነባ በሚገኘው ‘ኤል ዳባ’ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማብላያዎች (ሪአክተሮች) ላይ "ከፍተኛ የግንባታ ጉድለት" መገኘቱን ተመርኩዞ የቀረበ ዘገባ በግብፅ፣ በሩሲያው ተቋራጭ ኩባንያ እና በሚዲያዎች መካከል ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል።

የአሜሪካው ‘ፖለቲኮ’ ጋዜጣ ያገኛቸውን የውስጥ ሰነዶች እና ምሥጢራዊ ደብዳቤዎችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፣ የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ባለሥልጣን ግንባታውን በሚያከናውነው የሩሲያው 'ሮሳቶም' ኩባንያ ላይ የደኅንነት አሠራር ጥሰት እና የግንባታ እንከኖች መኖራቸውን በመጥቀስ ክስ አቅርቧል።

እንደ ፖለቲኮ ዘገባ ከሆነ ከማብላያ ቁጥር 4 የብረት ልባስ በስተጀርባ ክፍተቶች መገኘታቸውን እንዲሁም በቀሪዎቹ ማብላያዎች መሠረት ንጣፎች ላይ ጉድለቶች የታዩ ሲሆን፣ ይህንኑ አስተካክሎ ለመጠገን ብቻ አንድ ዓመት ገደማ ወስዷል። በተጨማሪም ሮሳቶም የፕሮጀክቱ ግንባታ ከግማሽ በላይ መጠናቀቁን ለማሳየት አሳሳች ዘዴዎችን ተጠቅሟል በሚል የተከሰሰ ሲሆን፣ የውስጥ ሰነዶችም የመጀመሪያው ማብላያ ሥራ የሚጀምርበት ጊዜ በ18 ወራት ገደማ ሊራዘም እንደሚችል ያመላክታሉ።

የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ባለሥልጣን በበኩሉ የፖለቲኮ ዘገባ ትክክለኛና ሚዛናዊ ያልሆነ ምሥል አቅርቧል ሲል አስተባብሏል። ተቋሙ ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ እንደ ኤል ዳባ ባሉ ግዙፍና ውስብስብ ፕሮጀክቶች ላይ የቴክኒክ ምልከታዎች እና ማስተካከያዎች መደረጋቸው የመደበኛ አሠራር አካል እንደሆነ ገልጾ፣ ግንባታው በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ቁጥጥር እና የደኅንነት መስፈርት መሠረት እየተከናወነ ይገኛል ብሏል።

ክሱ የቀረበበት ሮሳቶም በበኩሉ የተሰነዘሩት ክሶች በኮንትራትና በቴክኒክ አሠራሮች የተረጋገጡ አይደሉም ሲል ያስተባበለ ሲሆን፣ የዘርፉ ባለሙያዎችም ፕሮጀክቱ ገና በማቋቋም ላይ በመሆኑ እና ማብላያዎቹ ሥራ ባልጀመሩበት ሁኔታ የራዲዬሽን አደጋ እንደሌለ አስረድተዋል።

በአጠቃላይ 28.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበትና 4,800 ሜጋዋት የማመንጨት አቅም የሚኖረው የኤል ዳባ ፕሮጀክት፣ አራት 'VVER-1200' ማብላያዎችን የሚያካትትና 25 ቢሊዮን ዶላሩ በሩሲያ ብድር የሚሸፈን ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በግብፅ ግንባታውን የሚያከናውነው 'ሮሳቶም' ኩባንያ በኢትዮጵያ የሚገነባውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም ለማከናወን ውል ገብቷል።

በመስከረም 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ሮሳቶም የትግበራ መርሃ ግብር ሞስኮ ውስጥ የተፈራረሙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገነባው ማመንጫም ተመሳሳይ የሆኑ 'VVER-1200' ማብላያዎች እንደሚገጠሙለትና ለአሥር ዓመታት ለሚቆየው ግንባታ የቦታ ልየታ መከናወኑ ተገልጻል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ