አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ዜና / ዜና ትንታኔ

የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች

በዳንኤል ግዛው | August 8, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በኩል ባወጣው መግለጫ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀደም ሲል ከነበሩት ከ3 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መካከል ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን ወደ ቀድሞ ቀያቸው መመለስ መቻሉን እና በአሁኑ ወቅት በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙትን 942 ሺህ ገደማ ተፈናቃዮች በዘላቂነት ለማቋቋም "ዜሮ ተፈናቃይ" የሚል መርሃግብር ይዞ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ የችግሩን ስፋት፣ የስርዓታዊ አሰራር ክፍተቶችን እና በምድር ላይ ያለውን አጠቃላይ የደህንነት እውነታ ለመሸፈን የተደረገ ፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ ግልፅ ነው።

​የኮሚሽኑ የመሠረተ ልማቶችና የመልሶ ማቋቋም ዳይሬክተር አቶ ታዬ ጌታቸው በአሁኑ ወቅት በመጠለያ ውስጥ ያሉትን ተፈናቃዮች ቁጥር 942 ሺህ እንደሆነ ገልፀዋል። ይሁን እንጂ ይህ ቁጥር በይፋ በተመዘገቡ የመንግሥት መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙትን ብቻ የሚያሳይ እንጂ፣ ከዘመዶቻቸው እና ከተስተናጋጅ ማህበረሰብ ጋር ተጠግተው የሚኖሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን ሙሉ በሙሉ ያገለለ ነው።

ከዚህም በላይ፣ መንግሥት "ሁለት ሚሊዮን ሰዎችን መልሼ አቋቁሜአለሁ" በሚል ስኬቱን ሲያውጅ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች በቀጣይነት ባለው ግጭት ምክንያት በየቀኑ አዲስ የሚፈናቀሉትን ዜጎች ቁጥር ሙሉ በሙሉ ችላ ብሎታል። አዳዲስ ተፈናቃዮች እየተፈጠሩ ባሉበት ሁኔታ "ተፈናቃዮችን ጨርሰናል" የሚለው ትረካ ከእውነተኛው የስታቲስቲክስ እውነታ ጋር ይጋጫል።

​መንግሥት "ዜሮ ተፈናቃይ" የመፍጠር ዓላማ ሰንቆ እየሠራሁ ነው ማለቱ በራሱ መልካም ስም ቢሆንም፣ በተግባር ግን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ስጋት ደቅኗል። ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው የሚመለሱት ወይም የሚዛወሩት የተፈናቀሉበት ዋና ምክንያት ሲወገድ እና አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ሲኖር ብቻ መሆን አለበት።

አሁንም የዜጎች ህይወት በየቀኑ በሚያልፍባቸው እና የህግ የበላይነት ባልተከበረባቸው አካባቢዎች ተፈናቃዮችን "ቦታ ለማስናት" እና የመንግሥትን ገፅታ ለመገንባት ሲባል ብቻ ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ ማድረግ፣ ለአዲስ ጥቃት እና ለዳግም ተፈናቃይነት መዳረግ ነው። ዘገባው ስለ ደህንነት ዋስትና እና ስለ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሔ አንዳችም ነገር ሳያነሳ ስለ "ምልሰት" ብቻ ማወራቱ የመፍትሔውን ቅደም ተከተል ያዛባል።

​ኮሚሽኑ "በየወሩ አስፈላጊው የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ሰብዓዊ ድጋፎች እየቀረበ ይገኛል" ቢልም፣ በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን የተለየ ነው። በርካታ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት እና የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚገልፁት፣ በገንዘብ እጥረት እና በፀጥታ ምክንያት ወደ ተለያዩ መጠለያዎች የእርዳታ እህል በወቅቱ ማድረስ አልተቻለም።

ተፈናቃዮች በረሃብ እና በበሽታ እየተሰቃዩ ባሉበት ሁኔታ "በየወሩ በቂ ድጋፍ ይደርሳቸዋል" የሚለው ዘገባ የችግሩን ገዝፎ መውጣት የሚያስቅቡ ድምፆችን ለማፈን የተደረገ ፕሮፓጋንዳዊ መግለጫ ነው። በተጨማሪም፣ የወደሙ መሰረተ ልማቶች (ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የመጠጥ ውሃ) ባልተገነቡበት ሁኔታ ተፈናቃዮችን መመለስ እንዴት "ዘላቂ ማቋቋም" ሊባል እንደሚችል ዘገባው ያቀረበው ማብራሪያ የለም።

​በአጠቃላይ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ያቀረቡት ይህ ዘገባ የችግሩን ስር የሰደደ ፖለቲካዊ እና ደህንነታዊ መንስኤዎች ከመፍታት ይልቅ፣ የተፈናቃዮችን ቁጥር በማሳነስ እና "ዜሮ ተፈናቃይ" የሚሉ አዎንታዊ የሚመስሉ ቃላትን በመጠቀም የመንግሥትን ስራ ውጤታማ አስመስሎ ለማቅረብ የተደረገ ጥረት ነው።

ዘላቂ የመልሶ ማቋቋም ስራ የሚጀምረው ግጭቶችን ከማስቆም፣ የህግ የበላይነትን ከማስከበር እና የተፈናቃዮችን ሙሉ መብትና ደህንነት ከማረጋገጥ እንጂ፣ ቁጥሮችን በማጣመም እና የተሳሳተ የምስራች በመንዛት አይደለም።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ