“የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል”፤ መምህር ታዬ ቦጋለ | ከይር ታይምስ
አምዶች
የቅርብ ዜና
የመንገድ መሠረተ ልማት መስፋፋት የቱሪስት መዳረሻዎችን ሙሉ አቅም ለመጠቀም ፋና ወጊ ሚና ይጫወታል ተባለ የቤት ግንባታ ማዳሪጃ ደንብ (ለመንግስት ሰራተኞች) በቀጥታ ስርጭት፦ የናሳ (NASA) ጠፈርተኞች ከአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ወጡ የባይደን ትችት የዲሞክራቶችን እና የሪፐብሊካኖችን የፖሊሲ ልዩነት በድጋሚ ያጎላ ነው ተባለ ከታገደው የኢራን 12 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ስድስቱ ሊለቀቅ ነው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ዶ/ር ወንድወሠን አሠፋ መዝገብ ለተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ማደራጃ ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ; * የማረሚያ ቤት ኃላፊው ማብራሪያ እንዲሰጡ ታዘዘ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 76ኛው ዙር የመመረቂያ በዓል ላይ ያደረጉት ንግግር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲሱ የትምህርት ሪፎርም የሀገሪቱን መዋቅራዊ ስብራት ለመጠገን ወሳኝ መሆኑን ገለጹ አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ የኢራንን ይዞታዎች አጋየች! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ለቀጣዩ ሀገራዊ ውይይት መነሻ የሚሆኑ ዋና ዋና አጀንዳዎችን ይፋ አደረገ የመንገድ መሠረተ ልማት መስፋፋት የቱሪስት መዳረሻዎችን ሙሉ አቅም ለመጠቀም ፋና ወጊ ሚና ይጫወታል ተባለ የቤት ግንባታ ማዳሪጃ ደንብ (ለመንግስት ሰራተኞች) በቀጥታ ስርጭት፦ የናሳ (NASA) ጠፈርተኞች ከአለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ወጡ የባይደን ትችት የዲሞክራቶችን እና የሪፐብሊካኖችን የፖሊሲ ልዩነት በድጋሚ ያጎላ ነው ተባለ ከታገደው የኢራን 12 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ስድስቱ ሊለቀቅ ነው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ዶ/ር ወንድወሠን አሠፋ መዝገብ ለተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ማደራጃ ተጨማሪ ጊዜ ፈቀደ; * የማረሚያ ቤት ኃላፊው ማብራሪያ እንዲሰጡ ታዘዘ ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 76ኛው ዙር የመመረቂያ በዓል ላይ ያደረጉት ንግግር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲሱ የትምህርት ሪፎርም የሀገሪቱን መዋቅራዊ ስብራት ለመጠገን ወሳኝ መሆኑን ገለጹ አሜሪካ በሆርሙዝ ሰርጥ የኢራንን ይዞታዎች አጋየች! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ለቀጣዩ ሀገራዊ ውይይት መነሻ የሚሆኑ ዋና ዋና አጀንዳዎችን ይፋ አደረገ
ዜና / ዜና ትንታኔ

“የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል”፤ መምህር ታዬ ቦጋለ

ከይር ታይምስ | July 4, 2026

የታዋቂው የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ መምህር ታዬ ቦጋለ አረጋ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት እጅግ ጠንካራና ወቅታዊ መልዕክት፣ በአንዳርጋቸው ፅጌ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችና “የእንጨት ሽበት ነውረኝነት” ላይ ያነጣጠረ ስለታም ትንታኔ ሰንዝረዋል።

መምህር ታዬ በጽሑፋቸው፣ ዕድሜ ሁልጊዜም ለሀገርና ለወገን ማሰብን እንደማያወርስ በመጥቀስ፣ የያዘውን የታሪክ ስብራትና ጥላቻ ይዞ ወደ መቃብር አፋፍ እየተጓዘ ያለው ያ ዘመን ትውልድ ዛሬም ሀገርን ወደ ለየለት እልቂት ለመምራት ክብሪት እየጫረ መሆኑን በጥብቅ አስጠንቅቀዋል።

አንዳርጋቸው ፅጌ ከ50 ዓመታት በፊት በ24 ዓመት ወጣትነቱ ኢትዮጵያን ጥሎ በሱዳን በኩል መሰደዱን ያስታወሱት ታዬ ቦጋለ፣ ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ በድጋሚ በፖርት ሱዳን መድረክ ላይ ተገኝቶ ያደረገው ንግግር ግን እጅግ መርዘኛና አደገኛ መሆኑን አጋልጠዋል።

አንዳርጋቸው ሱዳንን “ባለውለታ” ካለ በኋላ፣ “የኢትዮጵያ መንግሥት ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (UAE) በመወገን ሱዳንን ለማፍረስ እየሠራ ነው” በማለት በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ለመለኮስ ያለመ ንግግር ማድረጉን ጠቅሰዋል። መምህር ታዬ “የእንግሊዝ (UK) ዜጋ የሆነውና ከሃምሳ ዓመታት በላይ ውጪ ሀገር የኖረው ይህ ግለሰብ በዚህ የጃጀ ዕድሜው ፖርት ሱዳን የተገኘው ማንን ወክሎ ነው?” ሲሉ ጠንካራ ጥያቄ ሰንዝረዋል።

መምህር ታዬ ቦጋለ አንዳርጋቸው ፅጌ “እኛም እንናገር፤ ትውልድ አይደናገር” በተሰኘው መጽሐፉ ያነገበውን ፍጹም ነውረኛ ጥላቻ ይፋ አድርገዋል። ግለሰቡ “አማራ የሚባል ብሔር የለም” ከማለቱም በላይ፣ የአማርኛ ቋንቋን “ወታደሮች ለምሥጢራዊ መግባቢያነት የፈጠሩት የወፍ ቋንቋ ነው” ሲል የገለጸበትን አግባብ በጥብቅ አውግዘዋል።

በተጨማሪም “ከዐድዋ ጦርነት በኋላ ዳግማዊ ምኒልክ የተሰዋውን ክርስቲያን ፍትሐት አስደርገው በክብር ሲያስቀብሩ፣ ሙስሊም ሰማዕታትን ግን ሥጋቸውን አሞራ እና ጅብ እንዲበላው በየሜዳው ጥለውት ሄዱ” በማለት አንዳርጋቸው ያስደጎሰው ጦማር፣ በኢትዮጵያውያን መካከል የማያባራ የሃይማኖትና የብሔር ቁርሾ ለመትከል የታለመ ስልታዊ የጥፋት ፖለቲካ መሆኑን የታሪክ ምሁሩ አረጋግጠዋል።

ታዬ ቦጋለ አንዳርጋቸው ፅጌ በትግራይ ወገናችን ላይ የዘር ማጥፋት (Genocide) ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደነበርና ነገ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕግ እንደሚጠየቅ ጠቅሰው፣ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ሊያፈርሱ የሚችሉ ኃይሎችን በአንድ ላይ የመጣመር አደገኛ ጥሪ እያቀረበ መሆኑን አጋልጠዋል፦

• ከአማራ ክልል መሬት የምትሻውን ሱዳንን፣

• ከትግራይ ሰፊ መሬት የሚፈልገውን ሻዕቢያን፣

• የወሰን ውዝግብ ያላቸውን ሕወሓትንና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን ኃይል በጽምዶ አጣምሮ ኢትዮጵያን የማፍረስ የተረገመ ጥሪ እያስተጋባ ይገኛል።

ታዬ ቦጋለ በጥያቄያቸው፡ “ይህ አረመኔ ግለሰብ ማንን ወክሎ ነው ይህንን ምስቅልቅል የሚፈጥረው? የለም ብሎ የካደውን አማራን? ሕወሓትን? ሻዕቢያን? ወይስ ሱዳንን?” ካሉ በኋላ፣ ምላሹን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመተው የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ባዳዎች በሕብረት በመጣመድ ሀገራችንን ወደለየለት እልቂት ለመምራት የተቀናጀ እቅድ ይዘው መነሳታቸውን አስገንዝበዋል።

የታሪክ ምሁሩ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሞት ሽረት ጥሪ አቅርበዋል። “ለውስጥ ፀቡ፣ ብሽሽቁና ልፊያው በኋላ እንደርስበታለን፤ ከሁሉም ሀገር ይቀድማል” ያሉት መምህር ታዬ፣ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ እንደሚያድር በማስታወስ፣ በአንድ ወቅት በቸልተኝነትና በስሜት የተረተረነውን ሀገር መልሰን በስሌት ለመስፋት ብንሞክር ዋጋው የከበደ እንደሚሆንና ሁላችንም የፀፀትን ዋጋ እንደምንከፍል አስገንዝበዋል።

ወጣቱ ትውልድ አፍ ከልብ ሆኖ ሀገሩን ለማዳን መሰለፍ እንዳለበት በመጠቆም፣ ከተንኮለኞች ሴራ ራሱን አርቆ ለመከላከያ ሠራዊታችን፣ ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት፣ ለፌደራል ፖሊስና ለመላው መለዮ ለባሾች እውቅናና ክብር በመስጠት ከሰላም ዘብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ