አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ዜና / የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ ለነባሩ አምባሳደር ሽሪ አኒል ኩማር ላይ ደሞቅ ያለ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት አከናወነ

በያፌት ግርማ | August 1, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

በአዲስ አበባ የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ የሥራ ባልደረቦች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ በኢትዮጵያ የሕንድ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሽሪ አኒል ኩማር እና ባለቤታቸው ሽሪማቲ ሃርሺታ ወደ አገራቸው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት በመዛወራቸው ምክንያት ደሞቅ ያለ የስንብት እና የሽኝት መርሃ-ግብር አዘጋጅተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

\r\n

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኤምባሲው ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው የሥራ ዘመን ላሳዩት አርአያነት ያለው አመራር፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ሁለገብ ግንኙነት ለማጠናከር ላበረከቱት አስተዋጽኦ፣ እንዲሁም ከባልደረቦቻቸው ጋር ለነበራቸው መልካም የወንድማማችነትና የቀረቤታ መንፈስ ያላቸውን የላቀ አክብሮት እና ምስጋና ገልጸዋል።

\r\n

​አምባሳደር ሽሪ አኒል ኩማር በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ በነበራቸው የዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ወቅት የኤምባሲው ዲፕሎማቶች እና የሥራ ባልደረቦች ላሳዩት ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነት፣ ትጋት እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አምባሳደሩ በአገልግሎት ዘመናቸው የኢትዮጵያን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር  የደገፉ ሲሆን፣ ሁለቱ አገራት በብሪክስ (BRICS) እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር (South-South Cooperation) ማዕቀፍ ውስጥ ያላቸውን ወዳጅነት ለማጠናከር ሲሰሩ ቆይተዋል።

\r\n

​ይህ የሽኝት መርሃ-ግብር በሕንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ታሪካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚገኝበት ወቅት የተከናወነ ነው። በአሁኑ ወቅት የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ንግድ ልውውጥ ከ550 ሚሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ከ675 በላይ የሕንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ከ6.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋል።

\r\n

በተጨማሪም የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያላቸው ዜጎች ያለቪዛ እንዲንቀሳቀሱ የተደረገው ስምምነት እና በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዲጂታል ዳታ ሴንተር ግንባታ ፕሮጀክት መጀመሩ የትብብሩን ጥልቀት ያሳያል።

\r\n

አምባሳደሩ ወደ አገራቸው ዋና መሥሪያ ቤት ተመልሰው ለሚያከናውኑት ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ የኤምባሲው ማህበረሰብ መልካም ምኞቱን ተመኝቶላቸዋል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ