አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ዜና / የሀገር ውስጥ ዜና

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ከብሔራዊ ደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ማዕቀብ ጣለ

በያፌት ግርማ | July 21, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ከሀገር አቀፍ የደህንነት ስጋቶች ጋር ተያይዞ በ92 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ገደብ እና እገዳ መጣሉን አስታወቀ። ከተለዩት ምርቶች መካከል 65ቱ በተወሰነ ገደብ እና በልዩ ፍቃድ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሲሆን፣ 27ቱ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ መሆናቸው ታውቋል።

​በአዲሱ መመሪያ መሠረት በተከለከሉት እና ገደብ በተጣለባቸው የቴክኖሎጂ ምርቶች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ቁሳቁሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፣ ወደ ውጭ መላክ ወይም መጠቀም በጥብቅ የተከለከለ ነው። እነዚህን ምርቶች መጠቀም የሚቻለው ከተቋሙ አስፈላጊውን የደህንነት ምረጣ፣ የምስክር ወረቀት እና ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ ተገልጻል።

​በዚህ የቁጥጥር ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ምርቶች መካከል የክብደት መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ድሮኖች፣ የሳተላይት ስልኮች፣ የጂ.ኤን.ኤስ.ኤስ (GNSS) መከታተያ መሳሪያዎች፣ የኔትወርክ አናላይዘሮች፣ የዲጂታል ፎረንሲክ መመርመሪያ ቁሳቁሶች እና ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸው ሰርቨሮች ይገኙበታል። እነዚህ መሳሪያዎች ለተለያዩ የሳይበር እና የብሔራዊ ደህንነት ስጋቶች ሊያጋልጡ ይችላሉ በሚል ስጋት ነው ውሳኔው የተላለፈው።

​እነዚህን የቴክኖሎጂ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም መጠቀም የሚፈልጉ አመልካቾች ስለ ምርቱ ዝርዝር መረጃ፣ ለምን ተግባር እንደሚያስፈልግ እና አግባብነት ያላቸውን ፈቃዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርም የቀረቡትን ጥያቄዎች መርምሮ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአካል የቴክኒክ ፍተሻ እንደሚያደርግ አስታውቋል።  

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ