አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ፖለቲካ / የፖለቲካ ፓርቲዎች

'ታሪክ ራሱን እንዳይደግም፤ አግላይ ምክክር ሳይሆን ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ መግባባት ይቅደም!' የኢሕአፓ መግለጫ

ኢ.ህ.አ.ፓ | July 19, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

ኢትዮጵያ ዛሬ ከባድ በሆኑ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት እና የማኅበራዊ ቀውሶች ውስጥ ትገኛለች። በየክልሉ የተስፋፉት አውዳሚ ጦርነቶች፣ የንጹሃን ሕይወት መጥፋት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች፣ የሕግ የበላይነት መፈራረስ፣ የኑሮ ውድነትና የተቋማት መዳከም በአጋጣሚ የተፈጠሩ አይደሉም። የብልጽግና ፓርቲ የተሳሳተ የፖለቲካ አቅጣጫና የሥልጣን አጠቃቀም ቀጥተኛ ውጤቶች ናቸው።

ኢሕአፓ በ2016 ዓ.ም. ከብልጽግና የምክክር ሂደት በይፋ የወጣው ሂደቱ ገለልተኛ፣ አካታችና ታማኝ እንዳልሆነ፣ ከመንግሥት ፍላጎት ውጭ ራሱን መምራት እንደማይችል እና የሕዝብን መሠረታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች የመፍታት ፈቃድም እቅድም እንዳልነበረው በመገንዘባችን ነበር። ዛሬ የተፈጠረው ሁኔታ ያኔ ያቀረብናቸው ስጋቶች ትክክል እንደነበሩ በግልጽ አረጋግጧል።

ብልጽግና ፓርቲ በአንድ በኩል የፖለቲካ ምህዳርን እየከረቸመ፣ እውነተኛ ተቃዋሚ ድምጾችን እያፈነ፣ በሌላ በኩል "ብሔራዊ ምክክር" በሚል ስም ራሱን የሰላምና የመፍትሔ ባለቤት አድርጎ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት የለየለት ፖለቲካዊ ተቃርኖ ነው። 

ቀውሱን የፈጠረ ኃይል በፍጹም ቀውሱን የሚፈታ ኃይል ሊሆን አይችልም። ችግሩን የፈጠረው አገዛዝ ራሱን እንደ መፍትሔ ለማቅረብ የሚያደርገው ጥረት የሀገሪቱን ቀውስ የበለጠ ከማራዘም በቀር ሌላ ውጤት አያመጣም።

ለአብነትም የደርግ ውድቀትን ተከትሎ የተካሄደው የሰላምና ዲሞክራሲ ጉባኤ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ እውነተኛ ብሔራዊ መግባባትና ምክክር ሳይፈጥር በመቅረቱ የሽግግር ሂደቱ መክሸፉን ማስታወስ ይቻላል።

እውነተኛ ምክክር የሚጀምረው በመተማመን ነው። መተማመን ደግሞ የሚመጣው የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ፣ ጦርነቶች ሲቆሙ፣ የሐሳብ ነፃነት ሲከበር፣ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች በእኩልነት ሲሳተፉ እና ሂደቱ ከገዢው ፓርቲ ተጽዕኖ ነፃ ሲሆን ነው።

እነዚህ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ የሚደረግ ምክክር ውጤቱ አስቀድሞ የተወሰነ የአንድ ግለሰብ እና ቡድን የፖለቲካ ትርኢት እንጂ የሀገር መፍትሔ አይሆንም።

ትግራይ፣ አማራ እና ከፊል የኦሮሚያ ክልሎች በዚህ ከመሰረቱ ጀምሮ ስሁት በሆነው የምክክር ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ላለመሆናቸው በክልሎቹ ውስጥ እየተካሄዱ ካሉት የቃላት እና የተግባር ጦርነቶች በተጨማሪ ከገዢው ፓርቲ በኩል ሀሳብ እና የትግል መንስኤ ላላቸው ዜጎች እና ቡድኖች የሚታየው የአግላይነት እና የማንአለብኝነት መንፈስ ማሳያም ውጤትም ነው።

ይህ ኮሚሽን ካቀረባቸው የውይይት ሃሳቦች መሀል ዛሬ የአብዛኛው የኢትዮጵያን ክፍል በከፍተኛ ደረጃ እየፈተነ ያለውን የጦርነት መቆምን ጥያቄ አያካትትም፡፡ 

በእርግጥ ከቀረቡት ዝርዝሮች መሀል የሰላም ጉዳይ ተነስቷል፡፡ ሆኖም በሕዝብ ላይ ያወጁትን የጥፋት ጦርነት ሳያቆሙ የሰላምን ጉዳይ ማንሳት ከለበጣ ጭውውት ያለፈ አንዳችም ፋይዳ የለውም፡፡

ለዚህም ነው የብልጽግና ፓርቲ 'ብሔራዊ' ምክክር የሀገርን ቀውስ ለመፍታት ሳይሆን የከሸፈውን የብልጽግና ፖለቲካዊ ቅቡልነት ለማደስ የተዘጋጀ መድረክ ነው የምንለው።

ኢትዮጵያ የምትፈልገው ይህ አይነቱን የፖለቲካ ዲስኩር ሳይሆን በፍትሕ፣ በተጠያቂነት፣ በእውነተኛ ዴሞክራሲና በሕዝብ ሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ እና የስርኣት ለውጥ ነው።

ብልጽግና የሀገር ሀብትን እንደልቡ በመበተን ሊያካሂድ የጀመረው "ብሔራዊ ምክክር" የብልጽግና ፓርቲና መሪዎቹን ለማዳን እንጂ ኢትዮጵያን ለማዳን አይደለም።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጋረጠበት የሕልውና አደጋ ለመዳን የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ጥሪያችንን እያቀረብን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ለፍትህ፣ ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲ እና ለእኩልነት ለሚደረገው ትግል ያለውን አጋርነት ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲቀጥል እንጠይቃለን።

ኢሕአፓ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ ለሕዝብ ሉዓላዊነትና ለፍትሕ የሚደረገውን ትግል በፅናት ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ - ኢሕአፓ
ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም 
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ