አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ፖለቲካ / ዲፕሎማሲ

የአፍሪካ ህብረት በስፔን እና ፈረንሳይ ለደረሰው የሰደድ እሳት አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለፀ

በአዳሙ እርቅይሁን | July 28, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በስፔን እና በፈረንሳይ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው አስከፊ የሰደድ እሳት አደጋ ያስከተለውን ሰብአዊ እና ቁሳቁስ ውድመት በመመልከት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ከተጎዱት ሀገራት ጎን መቆሙን አረጋግጧል።

ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም (July 28/2026) ከአዲስ አበባ የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ የህብረቱ ሊቀመንበር ክቡር አምባሳደር ማህሙድ አሊ የሱፍ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እንዲሁም ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች እና መንግስታት መፅናናትን ተመኝተዋል። 

አደጋው የሰው ህይወት ከማጠፉም በላይ በርካታ ዜጎችን ከቀያቸው ያፈናቀለ፣ በንብረት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ከፍተኛ ውድመት ያደረሰ በመሆኑ ጥልቅ አዘን እንዳሳደረባቸው ገልፀዋል።

ሊቀመንበሩ አክለውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የፅኑ አየር ንብረት መዛባት እና ድንገተኛ አደጋዎች አለም አቀፍ ትብብርን የማጠናከር አስፈላጊነትን በግልፅ እንደሚያሳዩ አስገንዝበዋል። 

የአፍሪካ ህብረት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያለውን የጋራ አቋም መሰረት በማድረግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረጉ ጥረቶችን ማጠናከር፣ ለሁኔታው ምላሽ የሚሰጡ የአሰራር ስልቶችን ማስፋፋት እና የተገቡ የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ቃልኪዳኖችን መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም ለአደጋው በቀላሉ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራትን እና ማህበረሰቦችን መደገፍ የጋራ ሃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል።

በመጨረሻም፣ የአፍሪካ ህብረት ለስፔን እና ለፈረንሳይ አጋርነቱን አዲስ በማድረግ፣ ሁለቱ ሀገራት እና ህዝቦቻቸው ካላቸው ጠንካራ የመቋቋም አቅም በመነሳት ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ አልፈው በፍጥነት እንደሚያገግሙ ሙሉ እምነት እንዳለው ገልፀዋል። አደጋውን ለመቆጣጠር እና ለማገገም የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ስኬታማ እንዲሆኑ ህብረቱ አጋርነቱን አረጋግጧል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ