አምዶች
የቅርብ ዜና
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን አዎንታዊ ጎኖች ማደነቁንና የታዩ ጥሰቶችን መቃወሙን ገለጸ በግብፅ የመጀመሪያው የኒውክሌር ጣቢያ ግንባታ ላይ ጉድለት መገኘቱ ውዝግብ አስነሳ ኢራን በሆርሙዝ የባህር ወሰን ላይ ያላትን ይዞታ እያጣች መሆኑ ተገለጸ ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምዱ «እንደታቀደው ይቀጥላል» ስትል የትራምፕን ሃሳብ ውድቅ አደረገች የአዲስ አበባ ባለቤትነት ውዝግብ፡ በሀገራዊ ምክክሩና በፖለቲካው መድረክ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል የጋራ ማረጋገጫ ቡድን አባላት ምርጫና የአሰራር ደንቦች አዲስ ውዝግብ ማስነሳታቸው ተገለፀ በሃይማኖት ጉዳዮች እና ሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሙሉ መግባባት ተደረሰ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ የአንበሳ ባንክ ሙሉ በሙሉ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መረጠ የመንግሥት “ዜሮ ተፈናቃይ” መርሐግብር እና የተሸፈኑ እውነታዎች የአሜሪካ በግብፅ ላይ ያተኮረ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂ እያበላሸው ነው — ብሌን ማሞ ዲሪባ
ፖለቲካ / ዲፕሎማሲ

ጌታቸው ረዳ የሕወሃትን አዲሱን አካሄድ "የግዴለሽነት ቁማር" ሲሉ ተቹ

በሮቤል ሙላቱ | July 2, 2026
🔒 Log in or create an account to earn rewards for reading this article!

የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በሕወሃት (TPLF) ነባር አመራሮች ላይ እጅግ ጠንካራ እና ያልተጠበቀ ትችት ሰነዘሩ። ዛሬ በአለም አቀፉ አፍሪካ ሪፖርት (The Africa Report) መጽሔት ላይ ባወጡት ሰፋ ያለ መጣጥፍ፣ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት እየተከተለው ያለው የፖለቲካ መስመር "የግዴለሽነት ቁማር" (reckless gambling) መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው በመጣጥፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት፣ የሕወሃት ከፍተኛ አመራሮች ከኤርትራ መንግሥት እና ከተለያዩ የአገር ውስጥ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር "ስልታዊ አጋርነት" ፈጥረናል በሚል የተሳሳተ እሳቤ "ያልተገባ የልብ ልብ ተሰምቷቸዋል" ብለዋል። ይህ አዲስ ስሌት በትግራይ እና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ሆን ብሎ በማሻከር ለድርጅቱ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማስገኘት የሚደረግ ጥረት መሆኑን ጠቅሰው፣ ድርጊቱን "በትግራይ ሕዝብ ሕልውና ላይ የሚደረግ አደገኛ ቁማር" ሲሉ ፈርጀውታል።

ከዚህ ቀደም የሕወሃት ቁልፍ ሰው እና የክልሉ ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ ጌታቸው፣ በዚህ ጽሁፋቸው ላይ ያልተለመደ የፀፀት ንግግርም አክለዋል። ትግራይ አሁን ላይ ለወደቀችበት ዘርፈ ብዙ ቀውስ፣ መፈናቀል እና ሰብአዊ መከራ እርሳቸው ጭምር የድርሻቸውን የፖለቲካ ኃላፊነት እንደሚወስዱ በግልጽ አስፍረዋል። ይሁን እንጂ አሁን ላይ በድርጅቱ ውስጥ ያለው የፖለቲካ መንፈስ ከስህተት ከመማር ይልቅ፣ የግል እና የቡድን ጥቅምን ከሕዝብ ጥቅም ጋር አዳቅሎ የማቅረብ አባዜ እንደተጠናወተው ገልጸዋል። "የሕወሃት አመራር ቡድናዊ ጥቅሙን ከትግራይ ሕዝብ ጥቅም ጋር አብሮ ጨፍልቆ ማቅረቡ እጅግ አደገኛው ክስተት ነው" ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተዋል።

ይህ መጣጥፍ በሕወሃት ውስጥ ላለፉት ወራት ሲንተከተክ የነበረውን ክፍፍል ይፋ ያደረገ ነው። በአንድ በኩል አቶ ጌታቸው የሚመሩትና ለፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ቅድሚያ የሚሰጠው የ"ጊዜያዊ አስተዳደሩ" አንጃ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአቶ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የሚመራውና የድርጅቱን የበላይነት ለማስጠበቅ የሚታገለው የ"ፓርቲው" አንጃ መኖራቸው ይታወቃል። ጌታቸው በጽሁፋቸው የፓርቲው አመራሮች የሰላም ስምምነቱን አክብረው ከመንቀሳቀስ ይልቅ፣ አዲስ ግጭት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ትንኮሳዎችን እና የዲፕሎማሲ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም፣ የሕወሃት አመራር ካለፈው ጥፋት ተምሮ ወደ ሰላማዊ እና ገንቢ ፖለቲካ ካልተመለሰ፣ ክልሉን ዳግም ወደማይወጣበት የጦርነት እና የውድመት አዙሪት ሊመራው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ይህ የአቶ ጌታቸው ረዳ ግልጽ ትችት በትግራይ የፖለቲካ መረጋጋት ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ይኖረዋል? እንዲሁም የፌደራል መንግሥቱ ለዚህ አዲስ ፍጥጫ የሚሰጠው ምላሽ ምን ይሆናል? የሚለው የብዙዎች የትኩረት ነጥብ ሆኗል።

ጥያቄ፡ አቶ ጌታቸው ረዳ የሕወሃት አመራር ከኤርትራ ጋር "ስልታዊ አጋርነት" ፈጥሯል ማለታቸው፣ በቀጠናው ዲፕሎማሲ ላይ ምን አዲስ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብለው ያስባሉ?

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ